ፈረንሳይ 2018 | ኬንያ የኢትዮጵያ ተጋጣሚ ለመሆን ተቃርባለች

ፈረንሳይ በ2018 ለምታስተናግደው የአለም ከ20 አመት በታች ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ የቅድመ ማጣርያ ጨዋታዎች መደረግ ሲጀምሩ ወደ ቦትስዋና ያወናችው ኬንያ በሎባስቴ ስታድየም ቦትስዋናን ገጥማ 7-1 በማሸነፍ በቀጣይ ዙር ኢትዮጵያን ለመግጠም ተቃርባለች፡፡

ማርታ አሙንዮሌቴ እና ማርጆሌን ኔኬሳ ሁለት ሁለት ሲያስቆጥሩ ካንቲሀ ሺልዋትሶ ፣ ኮራዞኔ አኩዊኖ እና ዲያና ዋሴራ ቀሪዎቹን ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡

የመልሱ ጨዋታ ከ15 ቀናት በኋላ ሐምሌ 29 በኬንያታ ስታድየም የሚካሄድ ሲሆን ቦትስዋና ወደ ቀጣይ የማጣርያ ዙር ለማለፍ የተሸነፈችብን የግብ ልዩነት ማወራረድ ይጠበቅባታል፡፡

የዚህ ማጣርያ አሸናፊ በቀጣይ የማጣርያ ዙር ኢትዮጵያን የሚገጥም ይሆናል፡፡ ለ2016 የፓፓዋ ኒው ጊኒ የአለም ከ20 አመት በታች ሴቶች ዋንጫ ለማለፍ ተቃርባ በመጨረሻው የማጣርያ ዙር በጋና ተሸንፋ የቀረችው ኢትዮጵያ ለማጣርያው የሚረዳትን ቅድመ ዝግጅት እስካሁን አልጀመረችም፡፡

ፎቶ – በት/ቤቶች ውድድር የተገኘችውና በጨዋታው ሁለት ጎል ያስቆጠረችው ማርታ አሙንዮሌቴ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *