​ፋሲል ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ፋሲል ከተማ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ማስፈረሙን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስታውቋል፡፡ ዳዊት እስጢፋኖስ እና ብሩክ ግርማ ክለቡን የተቀላቀሉ ተጨዋቾች ናቸው፡፡

ዳዊት እስጢፋኖስ የአንድ አመት የኤሌክትሪክ ውሉን አጠናቆ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ለማምራት ከስምምነት ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም በግል ጉዳይ ምክንያት ክለቡን ሳይቀላቀል ቀርቶ ወደ ፋሲል ከተማ አምርቷል፡፡ የሰለሞን ገብረመድህን መልቀቅን ተከትሎ የማጥቃት እንቅስቃሴን የሚመራ ተጫዋች እጥረት የነበረበት የአጼዎቹ የአማካይ ክፍል በዳዊት መምጣት ይጠናከራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ብሩክ ግርማ ሌላው የክለቡ ፈራሚ ነው፡፡ በከፍተኛ ሊጉ ለኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ሲጫወት የነበረው ብሩክ በቀኝ መስመር ተከላካይ ስፍራ ላይ ሰኢድ ሁሴን በማይኖርባቸው ጨዋታዎች ላይ አማራጭ ይፈጥራል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

One thought on “​ፋሲል ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

  • July 25, 2017 at 4:56 pm
    Permalink

    እባካችሁ የቀድሞ የወላይታ ዲቻ እና የወልዲያ ከነማ ተጫዋች የነበረውን ጠንካራውንና በጣም ጎበዝ የሆነውን በሱፐር ሊጉ አለ የተባለውን ጠንካራውን የተከላካይ መሥመር ተጫዋች አስቻለው ዘውዴን ተመልከቱት የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ቢያንሥ እንኳን ሙከራ እንዲያደርግ ብትጋብዙት፤ ምክንያቱም የቡና፤የመከላከያ፤የመቀሌ ፤ፋሲል ከነማ እና የወልዲያ ቡድኖች ተጫዋቹን ቢመለከቱት በጣም ጠንካራ ሥለሆነ አደራችሁን ብታዩት በጣም ምርጥ የተባለ የተከላካይ መሥመር ተጫዋች ነው፡፡

Leave a Reply

error: