ዮናታን ከበደ ለአርባምንጭ ከተማ ፈረመ

አርባምንጭ ከተማ የመስመር አጥቂው ዮናታን ከበደን በአንድ አመት ውል አስፈርሟል፡፡

ዮናታን ባለፈው ክረምት አዳማ ከተማን ለቆ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሀዋሳ ከተማ በማምራት የውድድር አመቱን በክለቡ ያሳለፈ ሲሆን በተለይ በመጀመርያው የውድድር አመት አጋማሽ በጉዳት እምብዛም ጨዋታ ሳያደርግ ቀርቷል፡፡ ከክለቡ ጋር የነበረውን የአንድ አመት ውልም በስምምነት በማፍረስ ጉዞውን ወደ አርባምንጭ አድርጓል፡፡

የቀድሞው የኤሌክትሪክ እና ዳሽን ቢራ አጥቂ በክረምቱ ለአርባምንጭ ከተማ የፈረመ ሶስተኛው ተጫዋች ሆኗል፡፡ ሲሳይ ባንጫ እና ታዲዮስ ወልዴ ከዚህ ቀደም ክለቡን መቀላቀላቸው ይታወሳል፡፡

ዳንኤል መስፍን

ዳንኤል መስፍን

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ዳንኤል መስፍን ነኝ

ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ ምልክት ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ
ዳንኤል መስፍን

ዳንኤል መስፍን

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ዳንኤል መስፍን ነኝ ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ ምልክት ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *