ወላይታ ድቻ ሁለት ተጫዋቾች አስፈርሟል

በዝውውር መስኮቱ በርካታ ተጫዋቾችን እያስፈረሙ ከሚገኙ ክለቦች አንዱ የሆነው ወላይታ ድቻ ከከፍተኛ ሊግ ተጫዋቾችን አስፈርሟል። 

በሀዲያ ሆሳዕና ለረጅም ጊዜያት የቆየው ኄኖክ አርፊጮ ወደ ወላይታ ድቻ ያመራ ተጫዋች ነው።  የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ ሆሳዕና በ2008 ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ከረዱት ተጫዋቾች አንዱ የነበረ ሲሆን ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናትም ክለቡን በአምበልነት መርቷል። በሀዲያ ሆሳዕና የኄኖክ አጣማሪ የነበረው ታረቀኝ ተሰማ ሌላው የወላይታ ድቻ ፈራሚ ነው። ታረቀኝ በቀኝ እና በመሀል ተከላካይ ስፍራዎች መጫወት የሚችል ተጫዋች ነው። ሁለቱም ተጫዋቾች በሁለት ዓመት ኮንትራት ለመጫወት የተስማሙ ሲሆን ከከፍተኛ ሊጉ ፍፃሜ በኋላ ድቻን የሚቀላቀሉ ይሆናል።

በክረምቱ የሁለቱን ጨምሮ በአጠቃላይ 8 ተጫዋቾችን ያስፈረመው ወላይታ ድቻ ከከፍተኛ ሊጉ ፍፃሜ በኋላ አንድ ተጨማሪ ተጫዋች ዝውውርን ይፋ እንደሚያደርግ ተገልጿል።