ሴቶች ዝውውር | ድሬዳዋ ከተማ ሁለት የቀድሞ ተጫዋቾቹን አስፈረመ

በሴቶች ዝውውር ቀዝቀዝ ያለ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ሁለት የቀድሞ ተጫዋቾቹ የሆኑት ግብ ጠባቂዋ ሂሩት ደሴ እና ተከላካይዋ ትዝታ ገዛኸኝን ነው በሁለት ዓመት ውል ያስፈረመው።

ትዝታ በድሬዳዋ ከተማ የወጣቶች ውድድር ውድድር ላይ ከተገኘች በኃላ በድሬዳዋ ከተማ፣ መድን እና ደደቢት የተጫወተች ስትሆን ዳግም ከ5 ዓመት በኃላ የቀድሞው ክለቧን መቀላቀል ችላለች። ግብ ጠባቂዋ ሂሩት ደሴ ደግሞ ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ ክለብ ውስጥ መጫወት የቻለች ሲሆን ከእግር ኳስ ከራቀች በኃላ ዳግም ተመልሳ የቀድሞው ቡድኗን ተቀላቅላለች፡፡