የአሰልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ ቡና 0-1 ጅማ አባጅፋር

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ጅማ አባ ጅፋር በአዲስአበባ ስታዲየም ኢትዮጵያ ቡናን 1ለ0 በመርታት ደረጃውን ያሻሻለበትን ድል አስመዝግቧል። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኃላ የሁለቱ ቡድን ምክትል አሰልጣኞች ተከታዮን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

” በአራት ቀን ልዩነት እንደመጫወታችን ተጫዋቾቻችን ላይ ጫና በዝቷል ” ዮሱፍ አሊ – ጅማ አባ ጅፋር – ምክትል አሰልጣኝ

“ጨዋታው ተመጣጣኝ ነበር ፤ በአራት ቀን ልዩነት እንደመጫወታችን ተጫዋቾቻችን ላይ ጫና በዝቷል ፤ በዚህም የተነሳ በጉዳት እና በህመም ውስጥ ይገኛሉ። ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ በአንድ ቀን ልዩነት እየተጫወትን እንገኛለን። በዚህም የተነሳ በባለፈው ተጫዋቾች ቀይረን በማስወጣት ለዛሬው ጨዋታ ዝግጅት አርገናል፡፡ሁለታችንም ኳስን ተቆጣጥረን ለመጫወት ሞክረናል ፤ ኢትዮጵያ ቡና ከአምናው በተለየ በረጃጅም ኳሶች ቶሎ ወደ ጎል ለመድረስ እንደሚጫወቱ በተወሰኑ ጨዋታዎች መመልከት ችለናል ፤ ለዚህም ጥንቃቄ ወስደን ለመጫወት ሞክረናል፡፡”

“ለደጋፊዎች የሚመጥን ጨዋታ አላሰየንም” ገብረኪዳን ነጋሽ – ኢትዮጵያ ቡና – ምክትል አሰልጣኝ

“ጨዋታውን በአብዛኛው እንዳያችሁት ነው፤ ለመጫወት አቅደን የመጣነውን ጨዋታ ለመጫወት ሞክረናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንደዚህ አይነት ነገር ያጋጥማል ስለተዘጋጀህ ብቻ ታሸንፋለህ ማለት አይደለም ፤ ከጨዋታ በፊት በልምምድ ሜዳ ላይ የቴክኒክና የታክቲክ ዝግጅቶችን ብናደርግን እንደ አጋጣሚ ደግሞ የዛሬው ዓይነት ነገር ይገጥማል ፤ ይህ በእግርኳስ የተለመደ ነው፡፡ አንድ ቡድን ተሸነፈ ማለት አበቃለት ወይም ወጣ ማለት አይደለም ከዚህ ቀድም የሰበሰበውን ነጥብ በነዚሁ ተጫዋቾች ነው ፤ እንደአጋጣሚ ሆኖ ዛሬ አልተሳካልንም ለደጋፊዎች የሚመጥን ጨዋታም አላሰየንም፡፡ ቀሪ ብዙ ጨዋታዎች ከፊታችን አሉ በቀሪ ጨዋታዎች የተሻለ ነገር እናሳያለን፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *