የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዋሳ ከተማ 2-2 ፋሲል ከነማ

በሚሊዮን ኃይሌ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬም ሲቀጥል ሀዋሳ ከተማ ፋሲል ከተማን አስተናግዶ ሁለት አቻ ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“ተጨማሪ ሁለት እና ሶስት ግብ ማግባት እንችል ነበር” አዲሴ ካሳ – ሀዋሳ ከተማ

“ሶስት ተጫዋቾችን ለኦሊምፒክ ቡድኑ  ማስመረጣችን ተፅዕኖ ፈጥሮብናል። ሶስት ተጫዋቾችን ያስመረጠ ቡድን ጨዋታ አለማድረግ ይችላል። ግን እኛ ይህን አልፈለግንም ነበር። ምክንያቱም ያሳደግናቸውን ተጫዋቾች እድል መስጠት ስላለብን እና የአንድ ተጫዋች ትልቁ ግብ ለብሔራዊ ቡድን መጫወት ስለሆነ ከክለብ ጥቅም ይልቅ የሀገር ጥቅም አስበልጠናል።  ለኦሊምፒክ ቡድኑ የተመረጡትን ተጫዋቾች ተክተዉ የገቡት ጥሩ ተንቀሳቅሰዋል። በተለይም በቅርቡ ከተስፋ ያሳደግነው መስፍን ታፈሰ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደመጫወቱ እንጂ ያገኛቸውን አጋጣሚ ግብ ማድረግ ይችል ነበር። እነሱ በመጀመሪያዉ ግማሽ ያገኟቸውን እድሎች አግኝተው መጠቀም ችለዋል። በአንፃሩ ደግሞ እኛ በመጀመሪያዉ እና በሁለተኛው ግማሽ እድሎችን መፍጠር ችለናል። ልክ እንደነሱ መጠቀም ብንችል ተጨማሪ ሁለት እና ሶስት ግብ ማግባት እንችል ነበር። ”

“እዉነት ለመናገር ጨዋታዉ በጣም ከብዶን ነበር” ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ

ስለ ጨዋታው

እንደሚታወቀው አርቴፊሻል ሜዳ ላይ ነው የተጫወትነው። ቀኑን ሙሉ ፀሀይ ሲጠጣ የዋለ ጎማ ላይ መጫወት ምን ሊፈጥር እንደሚችል መገመት አይከብድም። ለዛም በምንፈልገዉ መንገድ መንቀሳቀስ አልቻልንም። ተጫዋቾች ከአቅማቸዉ በላይ ተጫውተዋል። ለኛ እውነት ለመናገር በጣም ጨዋታው ከብዶን ነበር። ”

ከጨዋታው በፊት የወዳጅነት ጨዋታ ማድረጋቸውፈጠረ ተፅዕኖ..

” ከአልሜሪክ ውጪ ሌላ የወዳጅነት ጨዋታም ብናገኝ የመጫወት ፍላጎት አለን። ምክንያቱም ከሀዋሳ ጋር እና ከሌሎች ጋር ብትጫወት ጥቅም የለውም። ዋናዉ አላማ የሀገሪቱን እግር ኳስ ማሳደግ እስከሆነ ድረስ ሀገሪቱ ከሌሎች ጋር ስትታይ ምን እንደምትመስል የወዳጅነት ጨዋታ ማድረጋችን ይህን ለማወቅ ይረዳናል እንጂ ምንም ጫና የለውም። ”


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *