አአ U-17 | አዳማ እና ኤሌክትሪክ በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፈዋል

የአአ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከ17 ዓመት በታች ውድድር የ12ኛ ሳምንት አራት ጨዋታዎች በዕለተ ቅዳሜ ሲከናወኑ አዳማ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሰፊ ግብ ልዩነት አሸንፈዋል።

5:00 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሜዳ ላይ በተደረገ ጨዋታ አዳማ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስን 5-1 አሸንፏል። አዳማ ከተማ ተስፋ በተጣለበት በፍራኦል ጫላ አራት፣ እንዲሁም ነቢል ኑሬ ተጨማሪ አንድ ግብ አዳማ ከነማ በሰፊ ግብ ልዩነት ቅዱስ ጊዮርጊስን 5 -1 አሸንፈዋልጰ የድንቅ ክህሎት ባለቤቱ ፍራኦል የውድድሩን ከፍተኛ ግብ አግቢነት እየመራ ይገኛል።

3፡00 ሰአት ላይ ኢ/ወ/ስ/አካዳሚ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ያገናኝው ጨዋታ በኢትዮ ኤሌክትሪክ 5-2 አሸናፊነት ተጠናቋል ።

በሌሎች ጨዋታዎች ሀሌታ አፍሮ ፅዮንን 2-1ሲያሸንፍ ሠለም በመከላከያ 2-0 ተሸንፏል።

ኢትዮጵያ መድን ከኢትዮጵያ ቡና የመድን ስራ አስኪያጅ አበባው ከልካይ ስርዓተ ቀብረቸው ዛሬ በመፈፀሙ ጨዋታው ነገ 06:00 ጃንሜዳ ይካሄዳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: