ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ |  የ28ኛ ሳምንት የቅዳሜ ጨዋታዎች

ዛሬ በሚደረጉ የሊጉ አራት ጨዋታዎች ዙሪያ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተናል።

ጅማ አባ ጅፋር ከ ኢትዮጵያ ቡና

ጅማ አባ ጅፋር ከ27 ቀናት በኋላ ወደ ሜዳ ሲመለስ የደረጃ ለውጥ ባይፈጥርለትም አራተኛ ደረጃ ላይ ወደ ተቀመጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ ለመቅረብ የሚረዳውን ጨዋታ በሊጉ አጋማሽ ከሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ጋር ያደርጋል። በአንፃሩ ጨዋታው ከረጅም ውዝግብ በኋላ ከመቐለ ጋር ማክሰኞ ዕለት ለተጫወቱት ኢትዮጵያ ቡናዎች ወደ ስድስተኛ ደረጃ ከፍ የማለት ዕድልን ሊያስገኝላቸው ይችላል። ጅማዎች አምበላቸው መስዑድ መሀመድ ከጉዳት የተመለሰላቸው ሲሆን የቀኝ መስመር ተከላካያቸው ዐወት ገብረሚካኤል መሰለፍ ብቻ አጠራጣሪ ሆኗል። በኢትዮጵያ ቡና በኩል ደግሞ ተመስገን ካስትሮ እና ሚኪያስ መኮንን በጉዳት ክሪዚስቶም ንታንቢ እና ሀሰን ሻባኒ ደግሞ በብሔራዊ ቡድን ጥሪ ምክንያት ከቡድኑ ጋር አይኖሩም። 

የእርስ በርስ ግንኙነት እና እውነታዎች

– ጅማ አባ ጅፋር ወደ በሊጉ ከቡና ጋር በተገናኘባቸው ሦስት  ጨዋታዎች አልተሸነፈም ፤ ሁለቱን በ2-0 እና 1-0 ውጤቶች አሸንፎ አንዴ ያለግብ ተለያይቷል።  

– ለ11ኛ ጊዜ ከአዲስ አበባ ስታድየም ውጪ የሚጫወተው  ኢትዮጵያ ቡና ሁለት የድል እና ሦስት የአቻ ውጤቶችን ሲያስመዘግብ ስድስት ጊዜ ተሸንፏል። 

– ጅማዎች በሜዳቸው 13 ተጋጣሚዎችን ያስተናገዱ ሲሆን ሽንፈት ሳይገጥማቸው ስድስቱን በድል ሰባቱን ደግሞ በአቻ ውጤት አጠናቀዋል። 

ዳኛ

– ጨዋታውን ተፈሪ አለባቸው በመሀል ዳኝነት ይመራዋል። እስካሁን በሰባት ጨዋታዎች በመሀል ዳኝነት የተመደበው ተፈሪ 38 የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመዝ አንድ የሁለተኛ ቢጫ ፣ ሁለት የቀጥታ የቀይ ካርዶች እና አራት የፍፁም ቅጣት ምት ውሳኔዎችንም አሳልፏል። 

ግምታዊ አሰላለፍ

ኢትዮጵያ ቡና (4-3-3)

ዋቴንጋ ኢስማ

ኃይሌ ገ/ትንሳይ – ወንድይፍራው ጌታሁን – ቶማስ ስምረቱ – ተካልኝ ደጀኔ

አስራት ቱንጆ – አማኑኤል ዮሀንስ – ዳንኤል ደምሴ

እያሱ ታምሩ – አቡበከር ናስር – አህመድ ረሺድ

ጅማ አባጅፋር (4-4-2) 

ዳንኤል አጄይ

ተስፋዬ መላኩ – ከድር ኸይረዲን – አዳማ ሲሶኮ – ኤልያስ አታሮ

ዲዲዬ ለብሪ – መስዑድ መሀመድ – ይሁን እንዳሻው – አስቻለው ግርማ

 ማማዱ ሲዲቤ – ኦኪኪ ኦፎላቢ

ሀዋሳ ከተማ ከ መከላከያ

ይህ ጨዋታ ለባለሜዳዎቹ በሰንጠረዡ አጋማሽ ሦስት ደረጃዎችን የማሻሻል አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ሲችል መከላከያን በሊጉ እንዲቆይ ሊረዱት ከሚችሉ እጅግ ወሳኝ ሦስት ጨዋታዎች አንዱ ነው። ጦሩ ከወራጅ ቀጠናው ያለችውን የአንድ ነጥብ ልዩነት ለማስጠበቅ ወይንም ለማስፋት ከሀዋሳ ሙሉ ነጥብ ይዞ መመለስ ይኖርበታል። ሀዋሳ ከተማ በደቡብ ፖሊሱ ጨዋታ በሁለተኛ ቢጫ እና በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ የወጡት አክሊሉ ተፈራ እና ምንተስኖት አበራን በቅጣት ገብረመስቀል ዱባለን ደግሞ በጉዳት የማይጠቀም ሲሆን ጉዳት የነበረበት ደስታ ዮሃንስ የመሰለፍ ጉዳይም አጠራጣሪ ሆኗል። የመከላከያ ቡድን ግን ከምንይሉ ወንድሙ የረጅም ጊዜ ጉዳት ውጪ ሌላ የሚያጣው ተጫዋች አይኖርም።

የእርስ በርስ ግንኙነት እና እውነታዎች

– ሁለቱ ቡድኖች 27 ጊዜ ተገናኝተው ሀዋሳ ከተማ 11 ጊዜ በማሸነፍ ቀዳሚ ሲሆን መከላከያ 7 ጊዜ አሸንፏል። በቀሪዎቹ 9 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። ሀዋሳ 28 ፣ መከላከያ 24 ጎሎችን አስቆጥረዋል።

– በሀዋሳ 13 ጨዋታዎችን ያደረጉት ሀዋሳ ከተማዎች ስድስቱን አሸንፈው በአምስቱ ሲሸነፉ በቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ ነጥብ ተጋርተዋል። 

– ከሜዳው ውጪ 12 ጨዋታዎችን ያከናወነው መከላከያ ሦስቱን በድል ሲወጣ በአራቱ ነጥብ ተጋርቶ ሲመለስ አምስት ሽንፈቶች ገጥመውታል።

ዳኛ

– ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት የተመደበው ቢኒያም ወርቅአገኘው ነው። አርቢትሩ በስምንት  ጨዋታዎች 37 የማስጠንቀቂያ እና አንድ የቀይ ካርዶችን ሲመዝ ሦስት የፍፁም ቅጣት ምቶችን ሰጥቷል።
                                                                            ግምታዊ አሰላለፍ

ሀዋሳ ከተማ (3-5-2)

ሶሆሆ ሜንሳህ

አዲስዓለም ተስፋዬ – መሣይ ጳውሎስ – ላውረንስ ላርቴ

                                                              
ጌትነት ቶማስ – አስጨናቂ ሉቃስ – ሄኖክ ድልቢ – ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን – ያኦ ኦሊቨር

አዳነ ግርማ – መስፍን ታፈሰ

መከላከያ (4-2-3-1)

አቤል ማሞ

ሽመልስ ተገኝ – ምንተስኖት ከበደ – አዲሱ ተስፋዬ – ታፈሰ ሰረካ

በኃይሉ ግርማ – ቴዎድሮስ ታፈሰ 

ፍፁም ገ/ማርያም – ዳዊት እስጢፋኖስ – ፍሬው ሰለሞን

 ፍቃዱ ዓለሙ

ስሑል ሽረ ከ ደደቢት

ስሑል ሽረ በሊጉ የመቆየት ተስፋውን ለመጨመር የሚረዳውን ጨዋታ መውረዱን ካረጋገጠው ደደቢት ጋር ያከናውናል። በሜዳቸው የተሻለ ውጤት ላላቸው ሽረዎች ዋነኛ ተፎካካሪዎቻቸው መከላከያ እና ደቡብ ፖሊስ በዚህ ሳምንት  ከሜዳቸው ውጪ ጨዋታዎቻቸውን ማከናወናቸው ሲታሰብ ደግሞ ውጤቱ እጅግ አስፈላጊያቸው እንደሆነ መረዳት ይቻላል። ሽረዎች ዮናስ ግርማይን በቅጣት ከማጣታቸው በቀር ቀሪው የሁለቱ ተጋጣሚዎች ስብስብ በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛል።

የእርስ በርስ ግንኙነት እና እውነታዎች

– በመጀመሪያው ዙር የተገናኙበት ጨዋታ በሽረ 1-0 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ነበር።

– ስሑል ሽረዎች በሜዳቸው በስምንት ጨዋታዎች ነጥብ ሲጋሩ አንዴ የተሸነፉ ሲሆን በአራት ጨዋታዎች ደግሞ ድል ቀንቷቸዋል።     

– ከመቐለ ውጪ 11 ጨዋታዎችን ያደረገው ደደቢት መከላከያን ከረታበት ጨዋትታ በቀር ሌላ ነጥብ ማግኘት አልቻለም።   

ዳኛ

– አምስት ጨዋታዎችን ዳኝቶ 13 የማስጠንቀቂያ ካርዶችን እና ሁለት የፍፁም ቅጣት ምቶችን የሰጠው ሀብታሙ መንግስቴ ይህን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት የመምራት ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

ግምታዊ አሰላለፍ

ስሑል ሽረ ( 4-2-3-1)

ዳዊት አሰፋ

ዓብዱሰላም አማን – ክብሮም ብርሃነ – ዲሜጥሮስ ወ/ሥላሴ – ረመዳን የሱፍ

ብሩክ ተሾመ – ደሳለኝ ደባሽ 

ቢስማርክ አፖንግ –  ያስር ሙገርዋ – ቢስማርክ አፒያ

ሳሊፉ ፎፋና  

ደደቢት (4-2-3-1)

ሙሴ ዮሃንስ  

ሙሉጌታ አንዶም – ዳዊት ወርቁ – አንቶንዮ አቡዋላ – ሄኖክ መርሹ  

የአብስራ ተስፋዬ – ኤፍሬም ጌታቸው  

መድሀኔ ብርሀኔ – አቤል እንዳለ – ፉሰይኒ ኑሁ  

መድሃኔ ታደሰ

ባህር ዳር ከተማ ከ ወላይታ ድቻ    

በተመሳሳይ በ 09፡00 በሚጀምረው ሌላኛው የዛሬ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ወደ ስድስተኛ ደረጃ ለመድረስ ወላይታ ድቻ ደግሞ በቅርብ ርቀት ከሚገኙት ክለቦች ስጋት ለመራቅ የሚጠቅማቸውን ጨዋታ ያከናውናሉ። ህመም ላይ በሚገኙት አሰልጣኙ ጳውሎስ ጌታቸው ላይመራ የሚችለው ባህር ዳር ከተማ ምንተስኖት አሎ ፣ ማራኪ ወርቁ እና ልደቱ ለማን በጉዳት የማያሳለፍ ሲሆን ልምምድ የጀመረው ፍቅረሚካኤል ዓለሙ ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደ ሜዳ ሊመለስለት ይችላል። ወላይታ ድቻ ደግሞ አጥቂው ባዬ ገዛኸኝን በጉዳት እሸቱ መናን በቅጣት ሳቢያ በጨዋታው አያሰልፍም።

የእርስ በርስ ግንኙነት እና እውነታዎች

– በሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙበት የረንደኛው ዙር ጨዋታ 1-1 የተጠናቀቀ ነበር።

– በሜዳቸው በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ያለሽንፈት እየተጓዙ የሚገኙት ባህር ዳሮች ስምንት የድል እና አምስት የአቻ ውጤቶችን አስመዝግበዋል።

– ከሶዶ በወጣባቸው 14 ጨዋታዎች ድል ቀንቶት የማያውቀው ወላይታ ድቻ ስድስት ጊዜ ነጥብ ተጋርቶ ተመልሷል።

ዳኛ

– እስካሁን ስድስት ጨዋታዎችን የዳኘው ወልዴ ንዳው ይህን ጨዋታ እንዲመራ ተመድቧል። አርቢትሩ እስካሁን 32 የማስጠንቀቂያ ካርዶችን መዟል።

ግምታዊ አሰላለፍ

ባህርዳር ከተማ (4-3-3)

ሀሪሰን ሔሱ

ግርማ ዲሳሳ – ወንድሜነህ ደረጄ – አቤል ውዱ – ሳላምላክ ተገኝ

ዳንኤል ኃይሉ – ደረጄ መንግስቱ – ኤልያስ አህመድ

ፍቃዱ ወርቁ – ጃኮ አራፋት – እንዳለ ደባልቄ

ወላይታ ድቻ (4-2-3-1)

ታሪክ ጌትነት

ያሬድ ዳዊት – ደጉ ደበበ – ተክሉ ታፈሰ – ሄኖክ አርፌጮ

በረከት ወልዴ – ተስፋዬ አለባቸው

ፀጋዬ አበራ – አብዱልሰመድ ዓሊ – ቸርነት ጉግሳ

ኃይሌ እሸቱ

error: