ሴቶች ዝውውር | አቃቂ ቃሊቲ በርካታ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የነባሮችንም ውል አድሷል

በ2011 በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ቻምፒዮን በመሆን ወደ አንደኛ ዲቪዚዮን ያደገው አቃቂ ቃሊቲ አስር አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም አስራ ሶስት ነባር ተጫዋቾችን ውል ደግሞ አራዝሟል፡፡

ክለቡን በማሳደጉ ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸው አሰልጣኝ አብዱራህማን ዑስማን ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከሆነ ከየክለቡ መልካም የውድድር ጊዜ የነበራቸው አስር አዳዲስ ተጫዋቾችን ከማስፈረም ባለፈ አስራ ሶስት ነባር የቡድኑን ተጫዋቾች ውልም እንዳራዘሙ ተናግረዋል፡፡

ወደ ክለቡ የመጡ አዳዲስ ተጫዋቾች | ሽብሬ ካምቦ (ግብ ጠባቂ / ከኢትዮጵያ ቡና)፣ የውብዳር መስፍን (ተከላካይ / ከጌዲኦ ዲላ)፣ ፌቨን (ተከላካይ / ከኢትዮጵያ ቡና)፣ ገነት ፈረደ (ተከላካይ ከአአ)፣ ብርቄ አማረ (አማካይ / ከሻሸመኔ ከተማ)፣ በፀሎት መሐመድ (አማካይ/ ከጌዲኦ ዲላ)፣ መሀሪ በቀለ (አጥቂ/ከጌዲዮ ዲላ)፣ ትንቢት ሳሙኤል (አጥቂ /ከጌዴኦ ዲላ)፣ ሄለን መሰለ (አጥቂ /ፎቶ/አአ)፣ ፍቅርአዲስ (አጥቂ ከኢትዮጵያ ቡና)

ውል ያራዘሙ ተጫዋቾች | አዲስ ዳብራሞ (ግብ ጠባቂ)፣ ማህሌት ሺፈራው (ግብ ጠባቂ)፣ እየሩስ ታደሰ (ተከላካይ)፣ ዝናሽ መንክር (ተከላካይ) ማክዳ ዓሊ (ተከላካይ)፣ ሀና ተስፋዬ (ተከላካይ)፣ ዙፋን ደፈርሻ (አማካይ)፣ ንግስቲ ኃይሉ (አማካይ)፣ ዘነበች ቢርጉዋ (አማካይ)፣ አበራሽ (አማካይ)፣ ቤዛዊት ኃይሉ (አጥቂ)፣ ሰላም ጎሳዬ (አጥቂ)፣ ሰላም ኃይሌ (አጥቂ)


© ሶከር ኢትዮጵያ