የስፖርት ማሕበረሰቡ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ እና ለአቅመ ደካሞች የሚያደርገው ድጋፍ ቀጥሏል

የባሎኒ ህፃናት ማሰልጠኛ እና አሰልጣኝ ህይወት አረፋይነ ድጋፍ አድርገዋል።

የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን እና ወረርሺኙ ወደ ሀገራችን መግባቱን ከተሰማ በኋላ በርካታ የእግርኳሱ ቤተሰብ የገንዘብ እና የቁስ ድጋፍ በማድረግ ይገኛል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የመቐለ 70 እንደርታ ሴቶች ቡድን በማሰልጠን የምትገኘው ኢንስትራክተር ህይወት አረፋይነ እና ሁለት መቶ የሚጠጉ ህፃናት በማቀፍ በመንቀሳቀስ የሚገኘው ባሎኒ የህፃናት ማሰልጠኛ ማእከል በተናጠል ድጋፍ አድርገዋል። አሰልጣኝ ህይወት አረፋይነ በተወለደችበት አከባቢ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የሚውል የምግብ እና የንፅህና መጠበቅያ ድጋፍ ስታደርግ ባሎኒ አካዳሚዎችም በሀፍቱ ገብረእየሱስ አማካኝነት ለጎዳና ተዳዳሪ ህፃናት የምግብ እና የንፅህና መጠበቅያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ