ፋሲል ከነማ የወሳኝ ተጫዋቹን ኮንትራት አራዘመ

ፋሲል ከነማ የሱራፌል ዳኛቸውን ውል ለተጨማሪ ዓመታት ማራዘሙን ይፋ አድርጓል።

በ2010 ክረምት አዳማ ከተማን በመልቀቅ ወደ ፋሲል ካመራ በኋላ በክለቡ የተሳካ ጊዜ ማሳለፍ የቻለው ተጫዋቹ የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠ ሲሆን ከቡድኑ ጋር የጥሎ ማለፍ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫንም ማንሳት ችሏል። በኮሮና ወረርሺኝ ምክንያት ሊጉ እስከተሰረዘበት ወቅት ድረስ ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የቆየው ሱራፌል በክለቡ ያለው ውል ሰኔ 30 የሚጠናቀቅ በመሆኑ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በፋሲል ለመቆየት የሚያስችለውን ስምምነት ጎንደር በመገኘት በክለቡ ፅሕፈት ቤት በመገኘት እንደፈፀመ ለማወቅ ችለናል። ውሉ የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት ውሉ እንደሚፀድቅም ይጠበቃል።

ክለቡ በፌስቡክ ገፁ ጨምሮ እንደገለፀው አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ በቀጣይ ውላቸውን እንዲያራዝሙ እና አዲስ ክለቡን እንዲቀላቀሉ የሚፈልጓቸውን ተጫዋቾች ያሳወቁ ሲሆን የክለቡ አመራሮችም የአሰልጣኙን ጥያቄተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ አስታውቋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: