አዳማ ከተማ ሦስት ተጫዋቾች ለማስፈረም ተስማማ

አዳማ ከተማዎች ሁለት ተከላካዮች እና አንድ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ሲስማሙ የአንድ ተጫዋች ውልም ለማራዘም ተስማምተዋል። ወደ ቡድኑ የተቀላቀሉ ተጫዋቾችም ቶክ ጀምስ፣ ይበልጣል አዳሙ እና ቶማስ ወዳጆ ሲሆኑ ዳንኤል ተሾመ ውል ያራዘመ ተጫዋች ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ወልድያ እና መቐለ የሆነው የመሃል ተከላካዩ ቶክ ጀምስ በካፋ ቡና ሲጫወት የቆየ ሲሆን ወደ ፕሪምየር ሊጉ የሚመልሰውን ስምምነት አድርጓል።

ሌላው የመሐል ተከላካይ ይበልጣል አዳሙ ባለፈው ዓመት ከከፋ ቡና ጋር ጥሩ ዓመት ያሳለፈ ሲሆን ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ ውሃ ሥራ እና ናሽናል ሲሚንቶ ተጫውቷል።

ሦስተኛው ቡድኑን የተቀላቀለው እና ላለፉት ዓመታት ከብሄራዊ ሊግ ጀምሮ ከከፋ ቡና ጋር ቆይታ የነበረው ደግሞ ግብ ጠባቂው ቶማስ ወዳጆ ነው።

ሌላው ከቡድኑ ጋር ለመቆየት የተስማማው ደግሞ ግብ ጠባቂው ዳንኤል ተሾመ ነው። ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ የተጫወተው ይህ ግብ ጠባቂ በአዳማ ከተማ በቆየባቸው ላለፉት ሁለት ዓመታት በቂ የመሰለፍ ዕድል ባያገኝም በቀጣዩ የውድድር ዓመት በርካታ ጨዋታዎች ላይ እንደሚሰለፍ ይጠበቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: