ግዙፉ የግብ ዘብ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ተቃርቧል

ግዙፉ የግብ ዘብ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ተቃርቧል

ለአስራ ሁለት ወራት በኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታ የነበረው ጋናዊው ግብ ጠባቂ ወደ አዲስ አዳጊው ክለብ ለማምራት ተስማምቷል


የቅድም ውድድር ዝግጅታቸውን በባቱ ከተማ የጀመሩት እና በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ቡድናቸውን እያጠናከሩ የሚገኙት ነገሌ አርሲዎች አስቀድመው የዳዊት ተፈራ፣ በረከት ወልዴ ፣ ናትናኤል ሰለሞን እና ሀቢብ ከማልን ዝውውር ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ ግዙፉን ጋናዊው ግብ ዘብ ኢድሪሱ አብዱላሂን ለማስፈረም ተስማምቷል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በኢትዮ ኤሌትሪክ ቤት ጥሩ ቆይታ የነበረው የግብ ዘቡ በ30 ጨዋታዎች ተሳትፎ በማድረግ 2698 ደቂቃዎች በማገልገል በቡድኑ ውስጥ ብዙ ደቂቃዎች መጫወት የቻለ ቀዳሚ ተጫዋች ነው። ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣቱ አስቀድሞ በ2021/22 የውድድር ዓመት የቤኬም ዩናይትድ ቆይታው ካከናወናቸው 31 ጨዋታዎች በ18 መረቡን ሳያስደፍር በመውጣት የሊጉ ምርጥ ግብ ጠባቂ ሽልማት ሲያሸንፍ በመቀጠልም በታንዛንያው አዛም ቆይታ የነበረው ሲሆን አሁን ማረፍያው ነገሌ አርሲ ለማድረግ ነገ ከትውልድ ሀገሩ በመምጣት ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።