የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ነው፡፡ለማጠቃለያ ውድድር ማለፋቸውን ያረጋገጡ ቡድኖችም እየታወቁ ነው፡፡
በ10 ክለቦች መካከል የሚካሄደው የማጠቃለያ ውድድር ሰኔ ወር አጋማሽ ላይ በሀዋሳ የሚካሄድ ሲሆን ከመካከለኛ – ሰሜን ዞን 6 ፣ ከደቡብ-ምስራቅ ዞን ደግሞ 4 ቡድኖች ያልፋሉ፡፡
በዚህም መሰረት ደደቢት ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ማለፋቸውን ሲያረጋግጡ መከላከያ ከቀጣይ ጨዋታው 3 ነጥብ ካሳካ ሶስቱን ቡድኖች ይቀላቀላል፡፡ ሀዋሳ ከተማ ከተማ ደግሞ አቻ ውጤት ወደ ማጠቃለያው ለማለፍ በቂው ነው፡፡
የመካከለኛ – ሰሜን ዞን 16ኛ ሳምንት ውጤቶች
እሁድ ሚያዝያ 30 ቀን 2008
ዳሽን ቢራ 4-0 እቴጌ
ማክሰኞ ግንቦት 2 ቀን 2008
ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ 1-1 ኢትዮጵያ ቡና
ረቡዕ ግንቦት 3 ቀን 2008
ልደታ ክ/ከተማ 1-3 ቅዱስ ጊዮርጊስ
መከላከያ 0-0 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ማከሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2008
11፡30 ኤሌክትሪክ ከ ሙገር (አአ ስታድየም)
የ17ኛ ሳምንት ፕሮግራም
ቅዳሜ ግንቦት 6 ቀን 2008
09:00 ኤሌትሪክ ከ ኢትዮጵያ ቡና (አአ ስታድየም)
11:00 ሙገር ሲሚንቶ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (አአ ስታድየም)
እሁድ ግንቦት 7 ቀን 2008
09:00 መከላከያ ከ እቴጌ (አአ ስታድየም)
09:00 ዳሽን ቢራ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ጎንደር)
11:00 ደደቢት ከ ልደታ (አአ ስታድየም)
የደቡብ-ምስራቅ ዞን 8ኛ ሳምንት ፕሮግራም
እሁድ ግንቦት 9 ቀን 2008
09:00 አርባምንጭ ከተማ ከ ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ (አርባምንጭ)
09:00 ሲዳማ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ (ይርጋለም)
09:00 አዳማ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ (አዳማ)
የደቡብ-ምስራቅ ዞን 7ኛሳምንት ውጤቶች እና የደረጃ ሰንጠረዥን ይህን ሊንክ ተከትለው ይመልከቱ
soccerethiopia.net/?p=10179