ቡናማዎቹ ከተጫዋቾቻቸው ጋር ሊለያዩ ነው

ቡናማዎቹ ከተጫዋቾቻቸው ጋር ሊለያዩ ነው

በአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ የሚሰለጥነው ኢትዮጵያ ቡና ከአራት ተጫዋቾቹ ጋር ለመለያየት ተቃርቧል።

ኢትዮጵያ ቡና የ2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአንደኛ ዙር ውድድሩን በ23 ነጥብ አስራ ሦስተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁ ይታወቃል። በሁለተኛው ዙር የተሻለ ቡድን ይዞ ለመቅረብ አሰልጣኙ ባቀረቡት ዕቅድ መሠረት በቡድኑ ውስጥ ብዙም አበርክቶ ካልነበራቸው አራት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ለመለያየት መቃረባቸውን አውቀናል።

ከቡድኑ ጋር የሚለያዩት ቴዎድሮስ በለጠ፣ ተከተል በዙ ፣ ኪሩቤል ደሳለኝ እና ዩጋንዳዊው አጥቂ ሻባን መሐመድ ናቸው። ቴዎድሮስ እና ተከተል ባሳለፍነው ዓመት ከተስፋ ቡድን ወደ ዋና ቡድን ያደጉ ሲሆን ከቀድሞ አሰልጣኝ ዐቢይ ጋር ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ አብረው ማንሳታቸው ይታወቃል።

ሌላኛው ተጫዋች በአሜሪካን ሀገር ከነበረው የዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ጨዋታዎች ተመርጦ በ2015 ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በፋሲል ከነማ ተጫውቶ የነበረው ኪሩቤል ደሳለኝ ሲሆን ባሳለፍነው ዓመት በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ካደረገው የአስራ ስምንት ወራት ቆይታ በኋላ የሚለያይ ይሆናል።

እንዲሁም ለኢትዮጵያ ቡና ለአንድ ዓመት ለመጫወት ተስማምቶ የነበረው ለሀገሩ ክለብ ኦንዱፓራካ ፣ ካምፓላ ሲቲ ፣
ለቫይፈርስ ፣ ለኦንዱፓራካ ፣ ለካምፓላ ሲቲ ፣
ለሞሮኮ ራጃ ካዛቢላንካ ፣ ለሊቢያው አል ህላል እና አንዋር ተጫውቶ ያሳለፈው የዩጋንዳ ዋና ብሐራዊ ቡድን የፊት መስመር አጥቂው የነበረው መሐመድ ሻባን ከስድስት ወር ቆይታ በኋላ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በስምምነት የሚለያይ ይሆናል።

አሰልጣኝ ሳምሶን ከተጫዋቾች ጋር ከተለያዩ በኋላ በቀጣይ ቡድኑን ለማጠናከር አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው ይቀላቅላሉ ተብሎ ይጠበቃል።