የአዲስ አበባ ስታዲየም ትራክ ባለማለቁ የ25ኛ ሳምንት ወደ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የተዘዋወረው ውድድር በቀጣይ የት እንደሚካሄድ ሶከር ኢትዮጵያ አጣርታለች።

ከ25ኛው ሳምንት ጀምሮ የ2018 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በአዲስ አበባ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ አስቀድሞ መርሐ ግብር ወጥቶ ነበር። በአዲስ አበባ ስታዲየም ለማካሄድ ቀደም ብሎ ፕሮግራም የተያዘለት 25ኛ ሳምንት ውድድር የአዲስ አበባ ስታዲየም ትራክ ስላላለቀ ወደ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በመዘዋወር ውድድሩ መካሄዱም ይታወሳል። የውድድሩ ባለቤት ሊግ ካምፓኒው ከ26ኛ ሳምንት በኋላ ያለው መርሃ ግብር እና የመጫወቻ ሜዳ በፊት በወጣው (በአዲስ አበባ ስታዲየም) እንደሚቀጥልም ገልፆ ነበር።
ሆኖም ሶከር ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮቿ ባደረገችው ማጣራት የአዲስ አበባ ስታዲየም ትራክ አሁንም ተሰርቶ እንዳላለቀ እና 26ኛው ሳምንት ውድድር በዛው አበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚቀጥል ሰምታለች።

