ተጠባቂውን ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

ተጠባቂውን ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

በነገው ዕለት የሚደረገውን የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል።

ለ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ፍልሚያ የዕለቱን ጨዋታ በበላይነት የሚመሩት ዳኞች ይፋ ሆነዋል። በሊጉ ሻምፒዮና ሲዳማ ቡና እና በወልዋሎ ዓ/ዩ መካከል ነገ ሐሙስ ሐምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም በ5፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው ታላቅ የዋንጫ ጨዋታ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የመሐል እና የመስመር ዳኞች መድቧል።

በዚሁ መሠረት ጨዋታውን በዋና ዳኝነት እንዲመራ ኢንተርናሽናል ዳኛ ዳንኤል ይታገሱ የተመደበ ሲሆን መስመሩን ይዘው በረዳትነት የሚያግዙት ደግሞ 1ኛ ረዳት ኢንተርናሽናል ፋሲካ የኋላሸት እና 2ኛ ረዳት ኢንተርናሽናል ሙስጠፋ መኪ ሆነው ተመርጠዋል። በተጨማሪም ኢንተርናሽናል ዳኛ ሄኖክ አበበ የዕለቱ 4ኛ ዳኛ በመሆን ተመርጧል።
ይህ ከፍተኛ ትኩረት ያገኘው የሁለቱ ክለቦች የፍጻሜ ፍልሚያ በነገው እለት 5:00 ሲል በአዲስ አበባ ስታዲየም ጅማሮን ያደርጋል።