ጋቶች ፓኖም ወደ ጭልፊቶቹ አመራ

ጋቶች ፓኖም ወደ ጭልፊቶቹ አመራ

ኢትዮጵያዊው አማካይ የኩዌቱን ክለብ ተቀላቀለ

 

ባለፈው ዓመት መጀመርያ ኢትዮጵያ መድንን ከለቀቀ በኋላ በኢራቆቹን ክለቦች ኒው ሮዝ እና አል ናጃፍ እንዲሁም በሳውዲ ዓረብያው አል ዓረቢ ቆይታ ያደረገው ግዙፉ አማካይ ጋቶች ፓኖም ወደ ኩዌቱ ክለብ አል ፉሂሉ መቀላቀሉ ክለቡ በይፋዊ ገፁ ገልጿል።

ባለፈው የውድድር ዓመት አስር ቡድኖች በሚሳተፉበት ሊግ ላይ አምስተኛ ደረጃን ይዞ ካጠናቀቀ በኋላ ራሱን ለማጠናከር ቀደም ብሎ ራንጋ ቺቫቪሮ ፣ ዓሊ ፋደል ፣ ሐምዲ አልትዌል ፣ አብዱልአዚዝ ናጂ እና መሐመድ አልፋራሲ የተባሉ ተጫዋቾች ያስፈረመው ክለቡ ኢትዮጵያዊውን አማካይ ስድስተኛ ፈራሚውን በማድረግ ወደ ክለቡ ቀላቅሏል።