ነገሌ አርሲ ከአሰልጣኙ ጋር ይቀጥላል

ነገሌ አርሲ ከአሰልጣኙ ጋር ይቀጥላል

የሊጉ ክስተት የሆነውን ቡድን ያስመለከተን አሰልጣኝ ቱሉ ደስታ ከቡድኑ ጋር እንደሚቀጥል ታውቋል።

ወደ ሊጉ በመጣበት ዓመት በማይገመት ሁኔታ ጥቂት አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም አብዛኛውን ከከፍተኛ ሊግ ከቡድኑ ጋር የነበሩ ተጫዋቾችን በመያዝ የሊጉ ድንቅ ቡድን የሠራው አሰልጣኝ ቱሉ ደስታ ከክለቡ ጋር አብሮ እንደሚቀጥል አውቀናል።

የክለቡ የበላይ አካል አሁን አመሻሽ ላይ አጠናቆት በወጣው ስብሰባ አሰልጣኝ ቱሉ ደስታ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ከቡድኑ ጋር እንዲቀጥል መወሰኑን ስምተናል።

ነገሌ አርሲ ዘንድሮ እስከ መጨረሻው ድረስ በሊጉ በዋንጫ ፉክክር ውስጥ በመቆየት ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል።