ያሬድ ካሳዬ ለመቻል ፊርማውን አኑሯል

ያሬድ ካሳዬ ለመቻል ፊርማውን አኑሯል

ከሰዓታት በፊት ባደረስናቹህ መረጃ መሰረት የግራ መስመር ተጫዋቾቹ ጦሩን መቀላቀሉ እርግጥ ሆኗል

በ2019 የውድድር ዓመት ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን በርከት ያሉ ጠንከር ያሉ ዝውውሮችን እየፈፀሙ የሚገኙት መቻሎች የግራ መስመር ተከላካዩ ያሬድ ካሳዬን ለማስፈረም መቃረባቸውን መግለፃችን ይታወሳል። አሁን ባገኘነው መረጃ መሰረት ያሬድ ካዬ በሁለት ዓመት ውል በይፋ የጦሩ ተጫዋች ለመሆን ፌርማውን ማኖሩ ተረጋግጧል።

ያሬድ ያለፉትን አራት ዓመታ በኢትዮጵያ መድን ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡደን ድረስ ያገለገለ ሲሆን አሁን ደግሞ እናት ክለቡን በመልቀቅ መቻል እግርኳስ ህይወቱ ሁለተኛውን እንዲሆን ፌርማውን አኑሯል።