ላለፉት ሁለት ዓመታት በመቻል ቆይታ ያደረገው አማኑኤል ዮሐንስ በክለቡ ይቀጥላል

አስር ዓመት የቆየበትን አሳዳጊ ክለቡ ኢትዮጵያ ቡናን ከለቀቀ በኋላ ላለፉት ሁለት ዓመታት መቻልን ያገለገለው አማካዩ አማኑኤል ዮሐንስ በጦሩ ቤት ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለመቆየት ተስማምቷል። ቀደም ብሎ ያሬድ ካሳዬ ፣ ረመዳን የሱፍ እና አማኑኤል ተርፋን ለማስፈረም ተስማምቶ የአለምብርሃንን ውል ለማራዘም ከስምምነት የደረሰው ክለቡ በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ስብስቡን በማጠናከር ላይ ይገኛል።

