መቻሎች የመስመር ተከላካዩን ውል ለማራዘም ተስማምተዋል

አስቀድመው ያሬድ ካሳዬ፣ ረመዳን የሱፍ እና አማኑኤል ተርፉን ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመሩት መቻሎች አሁን ደግሞ የቀኝ መስመር ተከላካዩን ዓለምብርሀን ይግዛውን ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለማቆየት መስማማታቸውን አውቀናል። በእናት ክለቡ ፋሲል ከነማ ከጀመረው የእግርኳስ ህይወቱ በኋላ በመቻል ሃያ አራት ወራትን ያገለገለው ዓለምብርሃን ዳግም ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በጦሩ ለመቆየት መስማማቱ እርግጥ ሆኗል።

