አማኑኤል ተርፉ ዳግም ወደ ሊጉ ተመልሷል

አማኑኤል ተርፉ ዳግም ወደ ሊጉ ተመልሷል

በኢራቅ ቆይታ የነበረው ተከላካይ ዳግም ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ተቃርቧል

በቅዱስ ጊዮርጊስ ዘለግ ያሉ ዓመታትን ካሳለፈ በኋላ በዘንድሮ የውድድር ዓመት በኢራቁ ክለብ አል ናፍጥር ባስራ ቆይታ የነበረው ተከላካዩ አማኑኤል ተርፉ የውል ጊዜው ተጠናቆ ወደ ሀገር ቤት መመለሱ ይታወቃል። ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘቸው መረጃ አማኑኤል ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት ማሳየቱን ተከትሎ ከክለቡ ጋር ድርድር ያደረገ ሲሆን የተለየ ነገር ካልተፈጠረ ወደ መቻል የሚያደርገውን ዝውውር የሚያጠናቅቅ ይሆናል።