አብዱልከሪም ወርቁ በመቻል ይቆያል

አብዱልከሪም ወርቁ በመቻል ይቆያል

ስብስባቸውን ማጠናከር የቀጠሉት መቻሎች የወሳኝ ተጫዋቻቸውን ውል አራዝመዋል

በአዲሱ አሰልጣኛቸው ውበቱ አባተ የሚመሩት መቻሎች ለመጪው የውድድር ዘመን ስብስባቸውን በጠንካራ ሁኔታ ማጠናከራቸውን ቀጥለዋል። ቀደም ብለው አዲስ ፈራሚዎቹን ያሬድ ካሳዬ፣ ረመዳን የሱፍ እና አማኑኤል ተርፋን ለማስፈረም የተስማሙት ጦሮቹ በተጨማሪም የዓለምብርሃን ይገዛው እና የአማኑኤል ዮሐንስን ውል ማራዘማቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ የአብዱልከሪም ወርቁን ውል ማደሳቸውን ተከተሎ ክለቡ በዝውውር መስኮቱ ያለውን ንቁ እና ጠንካራ ተሳትፎ አጠናክሮ ቀጥሏል።

ላለፉት ሁለት ዓመታት በመቻል ስኬታማ ቆይታ ያደረገው አማካዩ አብዱልከሪም ወርቁ በክለቡ ለመቆየት ውሉን አራዝሟል። የእግር ኳስ ህይወቱን በኢትዮጵያ መድን በመጀመር በወልቂጤ ከተማ አሸብርቆ የወጣው እና በመቀጠል በኢትዮጵያ ቡና ቤት ድንቅ ጊዜያትን ያሳለፈው አማካዩ አብዱልከሪም ላለፉት ሁለት ዓመታት በጦሩ ቤት ጥሩ የወድድር ዓመታት ማሳለፍ የቻለ ሲሆን ተጫዋቹ አሁንም በቡድኑ ቤት ለመቆየት ተስማምቶ ውሉን ለማደስ ተስማምቷል።