አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ለ39 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ለ39 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ለሚያደርጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ዝግጅት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ለ39 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው መስከረም ወር ለሚያደርጋቸው የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ 10 የመጀመርያ ሁለት ጨዋታዎች ዝግጅት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ለ39 ተጫዋቾች ጥሪ ያደረጉ ሲሆን ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል ከ20 ዓመት በታች ናሽናል ካምፕ ላይ የሚገኙ 6 ተጫዋቾች ተካተዋል።

በዚህም መሠረት

ግብ ጠባቂዎች

አቡበከር ኑራ (ኢትዮጵያ ቡና)
ሰዒድ ሀብታሙ (ሀዋሳ ከተማ)
ፍሬው ጌታሁን (ድሬዳዋ ከተማ)
ትንሣኤ ማርቆስ (ሲዳማ ቡና U-20)

ተከላካዮች

ደግፌ ዓለሙ (ሲዳማ ቡና)
ሄኖክ አዱኛ (ሸገር ከተማ)
ፀጋአብ ግዛው (ሃዲያ ሆሳዕና)
ያሬድ ባየህ (ሲዳማ ቡና)
ሮኆቦት ሶላሎ (ነጌሌ አርሲ)
ራምኬል ጀምስ (ኢትዮጵያ ቡና)
አማኑኤል ተርፉ (መቻል)
ግሩም ሀጎስ (መቻል)
ነፃነት ገብረመድህን (ወልዋሎ ዓ/ዩ.)
ሳሙኤል ዮሐንስ (አዳማ ከተማ)
አብዱሰላም የሱፍ (ኢትዮጵያ ቡና)
ያሬድ የማነ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)

አማካዮች

ሀብታሙ ተከስተ (ኢትዮጵያ ቡና)
ጋቶች ፓኖም (አል ፋሃዬል / ኩዌት)
ሀብታሙ ጉልላት (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
በረከት ወልዴ (ነጌሌ አርሲ)
ከነዓን ማርክነህ (አል አረቢ / ኩዌት)
ቢንያም በላይ (ሃዋሳ ከተማ)
ዳዊት ተፈራ (ነገሌ አርሲ)

አጥቂዎች

መስፍን ታፈሰ (ሲዳማ ቡና)
ፍፁም ጥላሁን (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ብርሃኑ በቀለ (ሲዳማ ቡና)
ቢንያም ፍቅሩ (ሸገር ከተማ)
ቸርነት ጉግሳ (መቻል)
ኢዮብ ገብረማርያም (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
አቤል ያለው (ሲዳማ ቡና)
ናትናኤል ዳንኤል (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ታምራት ኢያሱ (ፋሲል ከነማ)
ዳዋ ሁቴሳ (አዳማ ከተማ)

ከኢትዮጵያ 20 ዓመት በታች ናሽናል ካምፕ

ዳዊት ካሳው (ሸገር ከተማ)
ቢንያም አብርሃ (ሸገር ከተማ)
አሚር ሚስባህ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ቸርነት ኡፋይሳ (ወላይታ ድቻ)
ብሩክ እይላቸው (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
ቅዱስ ዳዊት (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ዓርብ ነሐሴ 8  ከ8፡00 ጀምሮ በጁፒተር ሆቴል በመሰባሰብ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።