በረከት ደስታ መቻል ጋር በስምምነት በመለያየት ወደ ሌላው የሊጉ ክለብ አምርቷል።

በመቻል ቆይታ የነበረው የመስመር አጥቂው በረከት ደስታ ከጦሩ ጋር የነበረውን ውል በስምምነት አፍርሶ ለሃዋሳ ከተማ ለመጫወት ስምምነት ፈጽሟል። ለአዲሱ የውድድር ዘመን ስብስባቸውን ለማጠናከር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉት ሀዋሳ ከተማዎች አሁን ደግሞ የፊት መስመራቸው ለማጠናከር የበረከት ደስታን ዝውውር አጠናቅቀዋል።
የእግር ኳስ ሕይወቱን ከአዳማ ከተማ ወጣት ቡድን የጀመረው በረከት ደስታ በመቀጠል የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ባሳካበት ፋሲል ከነማ እንዲሁም ያለፉትን ሁለት ዓመታት በመቻል ቤት ድንቅ ቆይታ ማድረጉ ይታወቃል። አሁን ደግሞ የሀዋሳ ከተማን ማሊያ በመልበስ በሐይቆቹ ቤት አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል።

