ሽረ ምድረ ገነት የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ጀመረ

ሽረ ምድረ ገነት የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ጀመረ

በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ የሚመሩት ሽረ ምድረ ገነቶች የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ጀምረዋል።

በ2010 ክለቡን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያሳደጉትን አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬን በድጋሜ በመቅጠር በዝውውር መስኮቱ መክብብ ደገፉ፣ ተካልኝ ደጀኔ፣ በኃይሉ ግርማ፣ ፀጋአብ ዮሐንስ፣ ቢንያም ላንቃሞ፣ አዲስ ተስፋዬ፣ ስንታየሁ ዋለጬ፣ አቤል ማሙሽ፣ ሽመክት ጉግሳ እና ዳንኤል ዳርጌ ያስፈረሙት ሽረ ምድረ ገነቶች በመቀመጫ ከተማቸው ሽረ እንዳስላሴ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ጀምረዋል።

ባለፈው የውድድር ዓመት በሀያ ሰባት ነጥብ 16ኛ ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁት እና ለ2018 የውድድር ዓመት ቡድናቸውን ለማጠናከር በዝውውር መስኮቱ አስር አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረሙት ሽረ ምድረ ገነቶች በቀጣይ ቀናት የነባር ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ።