👉 “ስሜታዊ ሆኜ ላደረኩት ነገር በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ።”
👉 “አሰልጣኜን ገብረመድኅንን፣ ተጫዋቾችን ፣ ክለቡን እና መላውን የስፖርት ቤተሰብ ይቅርታ ማለት እፈልጋለሁ።”
ተቀይሮ ሲወጣ የለበሰውን መለያ በመወርወር ያልተገባ ባህሪ ያሳየው ያሬድ ካሳየ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።

በኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ሁለተኛ ጨዋታ ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በመደበኛ ክፍለ ጊዜ በሁለት አቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት ምርቶ ሲዳማ ቡና 4-3 ማሸነፉ ይታወቃል።
ከጨዋታው በላይ ትኩረት የሳበው እና የስፖርት ቤተሰቡን ያስቆጣው እና ያበሳጨው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የኢትዮጵያ መድን የግራ መስመር ተከላካይ የሆነው ያሬድ ካሳየ ተቀይሮ ሲወጣ አሰልጣኙን እና የቡድን አባላቱን ክብር በሚነካ መልኩ የሚለብሰውን ማልያ ወርውሮ መጣሉ ይታወሳል።
በዚህ ድርጊቱ የተፀፀተው ያሬድ ካሳየ ወደ ሶከር ኢትዮጵያ በመደወል የተፈጠረውን ድርጊት ይቅርታ በመጠየቅ ገልጿል።
“ስሜታዊ ሆኜ ላደረኩት ነገር በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ። ይህ ከእኔ የማይጠበቅ ነገር ነው። ለዚህም አሰልጣኜን ገብረመድኅንን ፣ ተጫዋቾችን ፣ ክለቡን እና መላውን የስፖርት ቤተሰቡን ይቅርታ ማለት እፈልጋለሁ። ባደረኩት ነገር በጣም ተፀፅቻለሁ። በማለት ሀሳቡን ገልጿል።

