ዋልያዎቹ ከዋልያ ቢራ ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ በሄራዊ ቡድን ከዋልያ ቢራ ጋር ከፍተኛ የገንዘብ ዋጋ ያለው የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ትላንት በተደገው ስምምነት ፌዴሬሽኑ ከዋልያ ቢራ በየአመቱ 14 ሚልዮን ብር የሚያገኝ ሲሆን በ4 አመቱ የኮንትራት ጊዜ በአጠቃላይ 56 ሚልዮን የኢትዮጵያ ብር ወደ ፌዴሬሽኑ ካዝና ይገባል፡፡

ዋልያ ቢራን የሚያስተዳድረው የአለም ቁጥር አንዱ የቢራ አምራች ኩባንያ ሄኒከን ከዚህ ቀደምም ከዋልያዎቹ ጋር በበደሌ ስፔሻል በኩል ለ2 አመታት የ24 ሚልዮን ብር ኮንትራት ያለው ስምምነት የነበራቸው ሲሆን የአሁኑ ኮንትራት አመታዊ 2 ሚልዮን ብር ጭማሪ አለው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *