የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቴክኒክ ዳሬክተር በመሆን ሲሰሩ የቆዩት ኢንስትራክተር መኮንን ኩሩ በራሳቸው ፍቃድ ከሃላፊነታቸው ለመልቀቅ የሚጠይቅ ደብዳቤ ባለፈው ሳምንት ማስገባታቸው ይታወሳል፡፡ የኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም የኢንስትራክተሩን ጥያቄ በመቀበል ከኢትዮዽያ እግር ኳስ ቴክኒክ ዳሬክተርነታቸው ማንሳቱን አሳውቋል።
መኮንን ኩሩን ተክተው በቀጣይ ጊዜያት የኢትዮዽያ እግር ኳስ ቴክኒክ ዳሬክተርነቱን ቦታ የሚረከበውን ግለበሰብ ፌዴሬሽኑ ያላሳወቀ ሲሆን በመጪዎቹ ቀናት ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡