የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ህዳር ላይ ይጀምራል

ማክሰኞ መስከረም 08 ቀን 2011

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሁለቱም ዲቪዚዮኖች የ2011 የውድድር ዘመን ህዳር 1 ቀን 2011 እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የአንደኛ ዲቪዝዮን ውድድር ቁጥሩ ዘንድሮ በሁለት ጨምሮ በ12 ክለቦች መካከል የሚከናወን ሲሆን በወረዱት ኤሌክትሪክ እና ሲዳማ ቡና ምትክ ጥረት፣ አርባምንጭ ከተማ፣ አአ ከተማ እና ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ የሚሳተፉ ይሆናል። የሁለተኛ ዲቪዝዮኑ ውድድር ደግሞ ካሉት 12 ቡድኖች በተጨማሪ አዳዲስ የሚቋቋሙ ቡድኖች እንደሚካተቱበት ቢጠበቅም ከፌዴሬሽኑ እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ አዲስ የሚመዘገቡ ክለቦች እንደማይኖሩና አምና በተወዳደሩት እና ከአንደኛ ዲቪዝዮኑ በወረዱት ክለቦች መካከል ይከናወናል።

ፌዴሬሽኑ የውድድሮቹ መጀመርያ ቢያሳውቅም ያለፈው ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት እና የዘንድሮው የእጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት የሚከናከንበትን ዕለት ገና እንዳልወሰነ ታውቋል።