ወላይታ ድቻ ኃይሌ እሸቱን አስፈረመ

ከሳምንት በፊት ከድሬዳዋ ከተማ ጋር የተለያየው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ኃይሌ እሸቱ ለወላይታ ድቻ ፈረመ፡፡

የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አጥቂ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ኤሌክትሪክን በመልቀቅ ነበር ወደ ድሬዳዋ ማምራት የቻለው። ወደ ምስራቁ ክለብ ካመራ በኃላ በአንድ ዓመት ውል የተቀላቀለው አጥቂው ቀሪ የስድስት ወራት ውል እየቀረው ከክለቡ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ ዛሬ ወደ ወላይታ ድቻ የሚያደርገውን ዝውውር አጠናቋል።

ኃይሌ እሸቱ በጦና ንቦቹ እስከ ዓመቱ መጨረሻ የሚያቆየውን ውል የፈረመ ሲሆን ከአላዛር ፋሲካ፣ አንዱዓለም ንጉሴ፣ ሳምሶን ቆልቻ እና ባዬ ገዛኸኝ ጋር ለተሰላፊነት ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *