ደሞዝ በአግባቡ የማይከፍሉ ክለቦች እንደሚታገዱ ተገለፀ

ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ደሞዝ በተገቢው መንገድ የማይከፍሉ ክለቦች እገዳ እንደሚጣልባቸው መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ተናገሩ።

በ2013 የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ሊጎች እንዲመለሱ ዛሬ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ከፕሪምየር ሊግ፣ ከከፍተኛ ሊግ እና ከሴቶች ክለብ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል። በውይይቱ ላይም መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ከደሞዝ አከፋፈል ጋር በተገናኘ ሃሳቦችን አንስተዋል።

“ከደሞዝ አከፋፈል ጋር በተያያዘ ክለቦች እንድታውቁ የምፈልገው ነገር አለ። ዘንድሮ በርካታ ክለቦች ለተጫዋቾቻችሁ ደሞዝ መክፈል ተስኗችሁ እንደነበር እናቃለን። ከዚህ በኋላ ግን ሁላችሁም በአቅማችሁ ነው ደሞዝ ለመክፈል መደራደር ያለባችሁ። በቀጣይ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለን አቋም ጠንካራ ነው። ከ2013 ጀምሮ ደሞዝ በአግባቡ የማይከፍል ክለብ እናግዳለን። ሁላችሁም በኪሳችሁ ልክ ብቻ ለመክፈል ጣሩ።”

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ