ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | የሀዋሳ እና አዳማ ጨዋታ ሳይካሄድ ቀረ

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ሀዋሳ ከተማ ከ አዳማ ከተማ ረፋድ አራት ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በአንድ ምክንያት ሳይካሄድ ቀረ፡፡

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ሀዋሳ ከተማ ከ አዳማ ከተማ ረፋድ አራት ሰዓት ጨዋታቸውን ለማድረግ ሁለቱም ሜዳ ላይ ቢገኙም የአዳማ ከተማ ቡድን የኮቪድ 19 ውጤት ይዞ ባለ መቅረቡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ሥራ አስፈፃሚ እና የውድድሩ መሪዎች ከሁለቱም ክለብ ተወካዮች ጋር ውይይት ካደረጉ በኃላ የእለቱ ዳኞች ወደ ሜዳ ሳይገቡ ጨዋታው ሳይካሄድ ቀርቷል። የዚህ ጨዋታ ውጤት እና ውሳኔ በደብዳቤ በቀጣይ ቀን እንደሚገለፅ የውድድሩ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው የማነ ብርሀን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ