ከፍተኛ ሊግ | ወልዲያ ከተማ በረከት ይስሀቅን እንዲሁም ስድስት ወጣቶችን አስፈረመ

በርካታ ተጫዋቾችን ከወር በፊት አስፈርሞ የነበረው ወልዲያ አጥቂው በረከት ይስሀቅን ጨምሮ ሰባት ተጫዋቾች አስፈርሟል፡፡

በከፍተኛ ሊጉ በምድብ ሀ ላይ የሚገኘው ወልድያ ከተማ አሰልጣኝ መኮንን ገብረዮሐንስን በቅጥር ማስታወቂያ ከቀጠረ በኋላ ከወር በፊት በርካታ አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን ማስፈረሙ ይታወሳል፡፡ ክለቡ አሁንም ተጠናክሮ ለመቅረብ በረከት ይስሀቅን ጨምሮ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡ የቀድሞው ሀዋሳ ከተማ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ደደቢት፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ደቡብ ፖሊስ እንዲሁም አምና ወደ ቀድሞ ክለቡ ኤሌክትሪክ ተጉዞ መጫወት የቻለው በረከት በአንድ ዓመት ውል ነው ወልድያን መቀላቀል የቻለው፡፡

ክለቡ ለአንድ ሳምንት ያህል በከተማው ያሉ ወጣቶችን በምልመላ ለመያዝ በማሰብ በአሰልጣኙ አማካኝነት ከተመለከተ በኋላ በስተመጨረሻም ስድስት የአካባቢው ወጣቶችን አስፈርሟል፡፡እነኚህም የተያዙት ወጣቶች ከተከላካይነት እስከ አጥቂነት መጫወት የሚችሉ ሲሆን እነርሱም አብርሀም ጌታቸው፣ ብሩክ ጌታቸው፣ ኃይሌ ጌታሁን፣ ሀብታሙ ሲሳይ፣ ዳግም ገብር እና ቴዎድሮስ ብርሀኑ ናቸው፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ