አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ሀምበሪቾ ዱራሜ ከ አዳማ ከተማ

በደረጃ ሠንጠረዡ አናት እና ግርጌ የተቀመጡ ክለቦችን የሚያገናኘውን ጨዋታ የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች እንዲህ ይቀርባሉ።

በሦስት ጨዋታ አንድም ነጥብ ያላሳካው ሀምበሪቾ ዱራሜ ከጅማ አባጅፋር ጋር ከተጫወቱበት ጨዋታ ሦስት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም ፀጋአብ ዮሴፍ፣ ነጋሽ ታደሰ እና ብሩክ ኤልያስ ወጥተው አምረላ ደልታታ፣ ቢኒያም ጌታቸው እና ተመስገን አሠፋ ገብተዋል። በተቃራኒው ከሌላኛው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከመጣው ክለብ ወልቂጤ ከተማ ጋር ጥሩ ፉክክር አድርጎ ነጥብ የተጋራው አዳማ ከተማ ደግሞ አንድ ለውጥ ብቻ አድርገዋል። በዚህም አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ በላይ ዓባይነህን አሳርፈው ኤሊያስ ማሞን ቋሚ አድርገዋል።

ፌዴራል ዳኛ ሄኖክ አክሊሉ የሚመራው የዕለቱ ጨዋታ ላይ ቡድኖቹ የሚጠቀሙት ቋሚ አሰላለፍ የሚከተለው ነው።

ሀምበሪቾ ዱራሜ

1 እሸቱ አጪሶ
3 ሙሉነህ ገ/መድህን
15 እንዳለ ዮሐንስ
4 ሮቦት ሰለሎ
11 መስቀሉ ለቴቦ
17 ተመስገን አሠፋ
14 አምረላ ደልታታ
8 ዋቁማ ዲንሳ
25 አቤኔዘር ኦቴ
12 ቢኒያም ጌታቸው
13 ዳግም በቀለ

አዳማ ከተማ

1 ሴኩምባ ካማራ
5 ጀሚል ያቆብ
20 ደስታ ጊቻሞ
28 አሚኑ ነስሩ
80 ሚሊዮን ሠለሞን
88 አሊሴ ጆናታን
8 በቃሉ ገነነ
25 ኤሊያስ ማሞ
26 ኤሊያስ አህመድ
27 ሠይፈ ዛኪር
10 አብዲሳ ጀማል