የጣና ሞገዶቹ ሦስተኛ ተጫዋቻቸውን አስፈርመዋል

በዛሬው ዕለት በይፋ ወደ ዝውውር ገበያው የገቡት ባህር ዳር ከተማዎች ሦስተኛ ተጫዋቻቸውን ወደ ስብስናቸው ቀላቅለዋል።

አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱን የሾሙት ባህር ዳር ከተማዎች ከአስር ቀን በፊት በተከፈተው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ላይ ዛሬ መሳተፍ ጀምረዋል። ከሰዓታት በፊት የተመስገን ደረሰን እና መሳኝ አገኘውን ዝውውር ጣገባደደው ክለቡም አሁን ፉአድ ፈረጃን አስፈርሟል።

ከአዳማ ተስፋ ቡድን አድጎ በዋናው ቡድን የጎመራው ፉአድ በዘንድሮ የውድድር ዘመን ወደ ሰበታ ከተማ አምርቶ ግልጋሎት መስጠቱ አይዘነጋም። ከክለቡ ጋር ያለው ውል መጠናቀቁን ተከትሎም በዛሬው ዕለት በይፋ ከቀድሞ አሠልጣኙ ጋር ዳግም ለመስራት ባህር ዳር ከተማን ተቀላቅሏል።