ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለአሰልጣኞቹ ጥሪ አድርጓል

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ዋና እና የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኙን ወደ መዲናው እንዲመጡ ጥሪ አስተላልፏል።

ከአራት ዓመት በኋላ በአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና እየተመራ ዘንድሮ በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እየተሳተፈ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌትሪክ እስካሁን ባደረጋቸው ሰባት ጨዋታዎች አንድ አሸንፎ በሁለት ጨዋታ ነጥብ ተጋርቶ በአራት ተሸንፎ አምስት ነጥቦችን በመያዝ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አስራ ሦስተኛ ላይ ይገኛል።

ከወቅታዊ ውጤት ጋር በተገናኘ ክለቡ በዛሬው ዕለት የቡድኑን ዋና አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና እና የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ መሐመድን በስልክ ጥሪ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጠርቷቸዋል።

ጥሪውን ተከትሎም ሁለቱም አሠልጣኞች ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ያቀኑ ሲሆን ነገ ለክለቡ የበላይ አካሎች ሪፖርት እንደሚያቀርቡ ሰምተናል። በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የሚኖሩ አዳዲስ ነገሮችን ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።