​ሀዋሳ ከተማ ጋናዊ ተከላካይ አስፈርሟል

በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ሀዋሳ ከተማ ጋናዊው የመሀል ተከላካይ ላውረንስ ላርቴን በአንድ አመት ኮንትራት አስፈርሟል፡፡

ተጫዋቹ ከ2008 ጀምሮ እስከ 2015 ለሀገሩ ክለቦች ናኒያ እና አሻንቲ ጎልድ የተጫወተ ሲሆን በ2015 ወደ ደቡብ አፍሪካው ክለብ አያክስ ኬፕታውን ከፈረመ በኋላ ሁለት የውድድር አመታትን አሳልፎ በዚህ ክረምት ወደ ቱኒዚያው ታላቅ ክለብ ክለብ አፍሪካን ቢያመራም በክፍያ ጉዳዮች ሳይስማሙ ውሉን በመቅደድ ያለፉትን ሁለት ወራት ክለብ አልባ ሆኖ ቆይቶ ነበር፡፡

ለጋና ብሔራዊ ቡድን አንድ ጊዜ መጫወት የቻለው ላርቴ የጋና ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን አምበልም መሆን ችሎ ነበር፡፡

አይቮሪኮስታዊው ተከላካይ ኮሊንስን ለሙከራ አስመጥቶ አመርቂ እንቅስቃሴ ባለማሳየቱ ኮንትራት ያልሰጠው ሲሆን የላርቴ መፈረም በተከላካይ መስመሩ ላይ መሳሳት የሚታይበት ሀዋሳ ከተማን ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *