ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሊያዊውን ተጫዋች አሰናበተ

ፈረሰኞቹ በክረምቱ ቡድኑን ከተቀላቀለው ማሊያዊ አጥቂ አቱሳይ ኒዮንዶ ጋር በስምምነት መለያየታቸውን አስታውቀዋል፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ ከሚገኙ አራት የውጪ ሀገር ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው የማሊ ዜግነት ያለው የ30 አመቱ አጥቂ አቱሳይ ኒዮንዶን በዘንድሮው የውድድር ዓመት በአንድ ጨዋታ ላይ ብቻ (47 ደቂቃዎች) የተሰለፈ ሲሆን ከአንደኛው ሳምንት በኋላም ከ18 ተጫዋቾች ዝርዝር ውጪ ሲሆን ቆይቷል። ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘችው መረጃ ጉዳት እያለበት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣቱና በሚፈለገው መልኩ ቡድኑን እያገለገለ የማይገኝ በመሆኑ በጋራ ስምምነት ከክለቡ ተሰናብቷል፡፡

ከ2007 ጀምሮ አብዛኛው የእግር ኳስ ህይወቱን በደቡብ አፍሪካ ያሳለፈው ይህ አጥቂ ዐምና በሁለተኛው የደቡብ አፍሪካ ሊግ ለሚሳተፈው ሻኩማ በተባለ ቡድን የስድስት ወራት ቆይታን ካደረገ በኋላ ነበር ቅዱስ ጊዮርጊስን በአንድ አመት የተቀላቀለው።


© ሶከር ኢትዮጵያ