የአሰልጣኞች አስተያየት | ወልቂጤ ከተማ 0-2 አዳማ ከተማ

በአስራ ሰባተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ የጨዋታ ቀን አዲስአበባ ስታዲየም ላይ ወልቂጤ ከተማን የገጠሙት አዳማ ከተማዎች 2-0 ድል ካደረጉት ጨዋታ መጠናቀቅ በኃላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ቡድን አባላት ተከታዮን ሀሳብ ሰጥተዋል።

“ብናሸንፍም በእንቅስቃሴ ረገድ ጨዋታው ያሰብነውን አይገልጽም” ደጉ ዱባሞ – የአዳማ ከተማ ም/አሰልጣኝ)

ስለጨዋታው

” በጨዋታው ያሰብነውን ያህል ኳሱን ተቆጣጥረን መጫወት አልቻልንም። በውጤት ረገድ ብናሸንፍም በእንቅስቃሴ ረገድ ጨዋታው ያሰብነውን አይገልጽም።”

በዛሬው ጨዋታ እቅዳቸው ስለነበረው

“እቅዳችን የነበረው ኳሱን ይዘን መጫወት ነበር። በጨዋታው ካሰብነው ረገድ ታክቲካሊ ተጫዋቾቻችን ሙሉ ለሙሉ አልተገበሩልንም ማለት እንችላለን። ሁላችንም የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ አለብን ብለን ነበር የገባነው። ውጤቱ ጥሩ ቢሆንም ጨዋታችን ረጃጅም ኳሶች ይበዙት ነበር።”

“ተጫዋቾቻችን በ90 ደቂቃ ውስጥ አቅማቸው የፈቀደውን አድርገዋል” ደግአረግ ይግዛው (ወልቂጤ ከተማ)
ስለ ጨዋታው

” በቅድሚያ አዳማዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እወዳለሁ። ተጫዋቾቻችን እንዳያችሁት በ90 ደቂቃ ውስጥ አቅማቸው የፈቀደውን አድርገዋል። በእግርኳስ ውስጥ ያልተጠበቀው ነገር ይከሰታል። በእርግጥ በመጀመሪያው 45 ብልጫዎች ተወስደውብን ነበር፤ በሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ ስህተቶቻችን አርመን የተሻለ ነገር ለመስራት ሞክረን ነበር። በዚህም በተደጋጋሚ ወደ ጎል መድረስ ብንችልም አጋጣሚዎችን መጠቀም አልቻልንም። ውጤቱን ለመቀልበስ ተጫዋቾች ባደረጉት ተጋድሎ እጅግ ደስተኛ ነኝ።”

© ሶከር ኢትዮጵያ