ድሬዳዋ ከተማ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ

ብርቱካናማዎቹ ግብ ጠባቂው ሀምዲ ጠፊቅን ሦስተኛ አዲስ ተጫዋች ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ 2010 መጫወት የጀመረው ይህ ግብ ጠባቂ በዛኑ ዓመት ግማሽ ላይ በውሰት ለናሽናል ሲሜንት ተሰጥቶ ተጫውቷል፡፡ በ2011 ለወልቂጤ ከተማ ፈርሞ በከፍተኛ ሊጉ ወልቂጤ ጥሩ ውጤት ይዞ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲገባ የካሜሩናዊው ግብ ጠባቂ ቢሊንጌ ኢኖህ ተጠባባቂ ሆኖ አሳልፏል።

አሰልጣኝ ደረጀ በላይን ተከትሎ ወደ ዲላ ከተማ ካመራ በኃላ ዘንድሮ በከፍተኛ ሊጉ እየተጫወተ የነበረው ይህ ግብ ጠባቂ ለቀጣዩ ዓመት የውድድር ዘመን ከሳምሶን አሰፋ፣ ፍሬው ጌታሁን እና ዛሬ ውሉን ለማደስ ከተስማማው ምንተስኖት የግሌ ጋር ለቋሚ ተሳላፊነት ይፎካከራል፡፡

ሀምዲ ቀደም ብለው ከተስማሙት አስጨናቂ ሉቃስ እና ሱራፌል ጌታቸው በመቀጠል ሦስተኛ የድሬዳዋ ከተማ አዲስ ተጫዋች ሆኗል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ