ዐፄዎቹ አጥቂ ለማፈረም ተስማሙ

ዐፄዎቹ አጥቂ ለማፈረም ተስማሙ

ታምራት ኢያሱ ወደ ፋሲል ከነማ ለማምራት ከስምምነት ደርሶ ዛሬ ስብስቡን ተቀላቀለ

የመጀመሪያውን ዙር በ33 ነጥቦች 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ያጠናቀቁት ፋሲል ከነማዎች የዝውውር መስኮቱ የመጀመሪያ ፈራሚያቸውን ለማግኘት ከስምምነት ደርሰዋል። ዐፄዎቹን ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሰው ተጫዋች ደግሞ ላለፈው አንድ ዓመት በአርባ ምንጭ ከተማ ቆይታ ያደረገው እና በውድድር ዓመቱ ሰባት ግቦችን ያስቆጠረው አጥቂው ታምራት ኢያሱ ነው። ከከፍተኛ ሊጉ ነገሌ አርሲ ከተገኘ በኋላ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በአርባ ምንጭ ከተማ የአንድ ዓመት ቆይታን ያደረገው አጥቂው ከአዞዎቹ ጋር የነበረውን ውል ከተጠናቀቀ በኋላ ፋሲል ከነማን ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱን ተከትሎ ዛሬ ቡድኑ ወደ ሚገኝበት ሆቴል መቀላቀሉ ሲታወቅ የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት በይፋ ፌርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።