በውድድር ዓመቱ መጀመሪያ ቡናማዎቹን የተቀላቀለው ተጫዋች ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።

በ23 ነጥቦች በ13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው የመጀመሪያውን ዙር ያጠናቀቁት ኢትዮጵያ ቡናዎች ከግብ ጠባቂው እንዳሻው እሸቴ ጋር በስምምነት እንደተለያዩ በይፋዊ ገፃቸው ይፋ አድርገዋል። በውድድር ዓመቱ በ 10 ጨዋታዎች ተሳትፎ 840′ ደቂቃዎች ቡናማዎቹን ያገለገለው ግብ ጠባቂው ከወላይታ ድቻ ተስፋ ቡድን ከተገኘ በኋላ በዋናው ቡድን ደረጃ በአሳዳጊ ክለቡ ወላይታ ድቻ፣ የካ ክ/ከተማ፣ ሀላባ ከተማ እንዲሁም በያዝነው የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ ቡና መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ቀሪ ውል እያለው ከቡናማዎቹ ጋር ለመለያያት ከስምምነት ደርሷል።

