ከደቂቃዎች በፊት አንተነህ ተፈራን የግሉ ያደረገው ባህር ዳር የቀድሞ ተጫዋቹን ዳግም መልሷል

በአሠልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመራው ባህር ዳር ከተማ ጥር 30 በተከፈተው የዝውውር መስኮት ራሱን ለመቀጠናከር እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለትም አንተነህ ተፈራን እስከ ቀጣይ ዓመት መጨረሻ ማስፈረሙን ዘግበን ነበር። አሁን ባገኘነው መረጃ ደግሞ አደም አባስ የክለቡ 2ኛ ፈራሚ ሆኗል። በኢትዮጵያ ወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ የተገኘው የቀድሞ የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጫዋች አደም ከዚህ ቀደም የጣና ሞገዶቹን ተቀላቅሎ ግልጋሎት የሰጠ ሲሆን አስከፊ ጉዳት አጋጥሞት ለበርካታ ወራት ያለክለብ ከቆየ በኋላ ዳግም ወደቤቱ መመለሱ እርግጥ ሆኗል።

