ሸገር ከተማዎች የፊት መስመራቸውን ማጠናከር ተያይዘውታል

ቀደም ብለው ቢንያም ፍቅሩን ወደ ቡድናቸው በመቀላቀል ከአንተነህ ተፈራ ጋር በስምምነት የተለያዩት ሸገር ከተማዎች አሁን ደግሞ የፊት መስመር ተጫዋቹ ዮሴፍ ታረቀኝን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል። ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ሀዋሳ ከተማን ለቆ ወደ መቻል በማምራት በቡድኑ የወራት ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ከጦሩ ጋር ለመለያየት ከተስማማ በኋላ ላለፉት ቀናት የሸገር ከተማን ስብስብ ተቀላቅሎ ልምምድ በመስራት ላይ የሰነበተ ሲሆን አሁን ደግሞ የዝውውር ሂደቱ መጠናቀቁን ተከትሎ በቀጣይ ቀናት ፌርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

