አሰልጣኝ ፋሲል ወደ አዳማ ከተማ አምርተዋል

አሰልጣኝ ፋሲል ወደ አዳማ ከተማ አምርተዋል

በቅርቡ ሀድያ ሆሳዕን ለማሰልጠን ተስማምተው የነበሩት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ወደ አዳማ ማቅናታቸው ታውቋል።

ያለፉትን ሁለት ዓመታት ቅዱስ ጊዮርጊስን በማሰልጠን የቆዩት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከፈረሰኞቹ ጋር ያላቸውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ስማቸው ከሌሎች ክለቦች ጋር ሲያያዝ ቢቆይም በቅርቡ ሀድያ ሆሳዕናን ለማሰልጠን ከስምምነት መድረሳቸው የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አባተ ተስፋዬ መረጃውን አድርሰውን ነበር።

ሆኖም ሶከር ኢትዮጵያ አሁን እንደረሳት መረጃ ከሆነ አሰልጣኝ ፋሲል ከአዳማ ከተማ ጋር ለመነጋገር ትናንት ወደ አዳማ በመጓዝ ከክለቡ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ያደረጉት ድርድር በጥሩ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ የቀድሞ ክለባቸውን ዳግም ለማሰልጠን መስማማታቸውን አውቀናል። አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም በቅዱስ ጊዮርጊስን፣ ባህር ዳር ከተማ ፣ አዳማ ከተማ እና መቻል ማሰልጠን መቻላቸው ይታወሳል።