ከሁለት ቡድኖች ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳው ሁለገቡ ተጫዋች አዲስ ክለብ አግኝቷል

አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በመሾም ጠንካራ ቡድን ለመንገባት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉት እና አስቀድመው የያሬድ ካሳዬን ዝውውር ለማጠናቀቅ የተስማሙት መቻሎች አሁን ደግሞ በተለያዩ ቦታዎች መጫወት የሚችለውን ሁለገቡ ረመዳን የሱፍ ለማስፈረም ከስምምነት እንደደረሱ አውቀናል። ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ በሱህል ሽሬ ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በኢትዮጵያ መደን መጫወቱ ሲታወቅ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ከኢትዮጵያ መደን ጋር የሊጉን ዋንጫ ከፍ አድርጎ ማንሳቱ ይታወሳል።

