ከደቡብ አፍሪካው ክለብ ቤድቬስት ዊትስ ከተለያየ ሳምንታትን ያስቆጠረው ኢትዮጵዊው አጥቂ ጌታነህ ከበደ ስሙ ከሌላው የደቡብ አፍሪካ ክለብ ብሎሞፎንቴን ሴልቲክ ጋር መያያዙን ሶከር ላዱማ ድረ-ገፅ ዘግቧል
፡፡ ለ2015/16 የውድድር ዓመት እራሳቸው እያጠናከሩ ያሉት ብሎሞፎንቴን ሴልቲኮች የጌታነህ ቀጣይ ማረፊያ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡
ካማልዲን አብራውን በካይዘር ቺፍስ የተነጠቁት ሲዊሌሌቹ ዓይናቸው ወደ ጌታነህ ጥለዋል፡፡ በአሰልጣኝ ክሊንተን ላርሰን የሚመራው ብሎሞፎንቴን ሴልቲክ በ2013 የጌታነህ ፈላጊ ክለቦች ከነበሩ መካከል አንዱ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ዩንቨርሲቲ ኦፍ ፕሪቶሪያ ሌላው የጌታነህ ፈላጊ ክለብ ነው፡፡ ለዊትስ 9 ግቦችን በሁለት ዓመታት ያስቆጠረው ጌታነህ ደቡብ አፍሪካ እንደሚቆይ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
ብሎሞፎንቴን ሴልቲክ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በደቡብ አፍሪካ ሊግ በ40 ነጥብ 7ኛ ሆኖ ጨርሷል፡፡